Skip survey header
Amharic

የግራሃም ጣቢያ (Graham Station) አካባቢ እቅድ የዳሰሳ ጥናት

የግራሃም ሰፈር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ቅርጽ እንዲኖረው ለመርዳት የሲያትል ከተማ በዚህ የ15 ደቂቃ የዳሰሳ ጥናት ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል። የወደፊቱን ለግራሃም መንገድ ጣቢያ (Graham Street Station) ሰፈር ዙሪያውን በተመለከተ አንድ የጣቢያ አካባቢ እቅድ እየፈጠርን ነው። የሕዝብ ክፍት ቦታን፣ መኖሪያ ቤትን፣ መጓጓዣን፣ እና በሰፈሩ
ያሉትን አነስተኛ የንግድ ሥራን ማቆየት እንዲቻል ለመርዳት እኛ ለእርስዎ ከሁሉ ይልቅ አስፈላጊ የሚሆንልዎትን የበለጠ ማወቅ እንፈልጋለን።

ይህ የዳሰሳ ጥናት እኛ በ2019 ከግራሃም ማህበረሰብ የሰማናቸውን ራዕይ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በጥልቀት በመግባት - የግራሃም መንገድ: በማህበረሰብ ሁለንትናዊ ተሳትፎ የሚካሄድ የሰፈር ራዕይ - ለወደፊት ሊተገበር የሚችል እና እርስዎ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች እና ራእይ የሚያንፀባርቅ የወደፊት መንገድ ለማረጋገጥ።

እባክዎን ይህ የዳሰሳ ጥናት የሚያተኩረው በጣቢያው አካባቢ ሰፈር ላይ እንጂ በጣቢያው በራሱ ላይ እንዳልሆነ ልብ ይበሉ። ሳውንድ ትራንዚት (Sound Transit) ጣቢያውን እስከ 2031 ለመገንባት እያቀደ ነው። ስለግራሃም መንገድ ጣቢያ ንድፍ እና ግንባታ የበለጠ ለማወቅ፣ እባክዎትን የሳውንድ ትራንዚትን ድህረ-ገፅ


ይጎብኙ።