በSouth King County የJapanese ጥንዚዛን በተመለከተ የመረጃ ልውውጥ እና የህክምና ተደራሽነት ለማሻሻል ያግዙ።
የWashington State የግብርና መምሪያ (Washington State Department of Agriculture, WSDA) ነዋሪዎች፣ የንብረት ባለቤቶች፣ ተከራዮች፣ የንግድ ድርጅቶች እና የማህበረሰብ አጋሮች ስለ Japanese ጥንዚዛ የሚሰጠውን መረጃ እና ነፃ የግቢ ህክምና ፕሮግራም እንዴት እንደሚመለከቱት ወይም ተሞክሮ እንዳላቸው ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው። የእርስዎ አስተያየት፣ መረጃ የሚጋራበትን መንገድ እንዲሁም ሰዎች ህክምናን በተመለከተ ውሳኔ ሲወስኑ የሚደረግላቸውን ድጋፍ ለማሻሻል ይረዳል። ስለ አጠቃላይ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ይህንን ሊንክ በመከተል ወደ የ2026 የሕክምና ዘዴዎች ድረ-ገጽ ይሂዱ።
የዳሰሳ ጥናቱ ከ8 እስከ 10 ደቂቃ ገደማ ይወስዳል። የትኛውንም ጥያቄ መዝለል ወይም በማንኛውም ጊዜ ማቋረጥ ይችላሉ። በዚህ ሂደት ለመሳተፍ ያደረጉት ውሳኔም ሆነ የሚናገሩት ማንኛውም ነገር፣ ለአገልግሎቶች ብቁነትዎን ወይም WSDA ንብረትዎን የሚያስተናግድበትን መንገድ አይነካም።
ብቁ ከሆኑ፣ እንደ አማራጭ የሚሰጠውን የ $25 ስጦታ ካርድ (በዲጂታል ወይም በእጅ የሚሰጥ) ለመቀበል የሚያስችል የእውቂያ መረጃ የሚሞላበት የተለየ ቅጽ ይቀርብልዎታል። የስጦታ ካርዱ ለጊዜዎ እና ላካፈሉት ሀሳብ የሚሰጥ ካሳ ነው። ይህ ከህክምናው ጋር ስለ መስማማት የሚሰጥ ክፍያ አይደለም፤ እንዲሁም ምንም አይነት አመለካከት ቢኖርዎትም ይህንን ሊያገኙ ይችላሉ።
ለዳሰሳ ጥናቱ የሚሰጡዋቸው መልሶች በማጠቃለያው ይተነተናሉ። የስጦታ ካርድ ለመላክ የሚሰበሰበው የዕውቅያ መረጃ፣ ከዳሰሳ ጥናት መልሶችዎ ተለይቶ ይቀመጣል።
ከዚህ ጥናት ጋር የሚያያዝ ማንኛውም ጥያቄ ወይም ስጋት ካለዎት፣ እባክዎ ከ Dr. Anthony Campbell በ anthonyc@athenaplace.com ይገናኙ።
የዳሰሳ ጥናቱ ለመጀመር፣ እባክዎ ከታች ያለውን "Next" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ።